Application ends: May 31, 2026
Apply Now

Job Description

SUPRVISER

ድርጅታችንን ወደ ከፍተኛ ስኬት ለመምራት በዲጂታል ዘርፍ ሰፊ እውቀት ያላቸውን፣ ከፍተኛ ተነሳሽነት ያላቸውን እና ልምድ ያላቸውን ባለሙያዎች ይፈልጋል። ይህ የሥራ መደብ የድርጅቱን አጠቃላይ አስተዳደር፣ የሽያጭ ስራዎችን እና የፕሮዳክሽን ሂደቶችን በብቃት መምራት ለሚችሉ ባለሙያዎች የተዘጋጀ ነው።
ልዩ ማሳሰቢያ፦ ይህ የሥራ መደብ ሰልጣኞችን ወይም በቂ ልምድ የሌላቸውን አያካትትም። አመልካቾች የድርጅቱን ነባር ሥራዎች ተረክበው ወዲያውኑ ማስቀጠል የሚችሉ፣ በአስተዳደርና ሽያጭ ዘርፍ የካበተ ልምድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።

ዋና ዋና ኃላፊነቶች
1. ስትራቴጂክ አመራር እና ማርኬቲንግ
• የድርጅቱን ዋና አንቀሳቃሽ የሆነውን የማርኬቲንግ ዘርፍ ውጤታማ ማድረግ።
• ድርጅቱን ትርፋማ የሚያደርጉ ፖሊሲዎችን እና ስትራቴጂዎችን ነድፎ መተግበር።
• የድርጅቱን የአጭርና የረዥም ጊዜ ዕቅዶች ለማሳካት የሰው ኃይልንና የሥራ ሂደቶችን መምራት።
2. የፕሮዳክሽን እና የሥራ ሂደት ቁጥጥር
• የፕሮዳክሽን ሥራዎች በታቀደላቸው ጥራትና ጊዜ መጠናቀቃቸውን ማረጋገጥ።
• እያንዳንዱ የሥራ ሂደት ለድርጅቱ ግብ ስኬት የበኩሉን አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን መከታተልና ሪፖርት ማቅረብ።
• የሠራተኞችን የሥራ ክንውን መገምገም እና የአሠራር ባህል እንዲጎለብት ማድረግ።
3. ፋይናንስ እና አስተዳደር
• የበጀት አጠቃቀምን መከታተል፣ አላስፈላጊ ወጪዎችን መቀነስ እና ትርፋማነትን ማረጋገጥ።
• ከፋይናንስ ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የግብርና የቀረጥ ክፍያዎች በወቅቱ እንዲከናወኑ ማድረግ።
• አዳዲስ ሠራተኞችን የመመልመል፣ የማሰልጠን እና የማስተዳደር ሥራዎችን ማከናወን።
የሚያስፈልጉ መስፈርቶች
• ትምህርት፡ የመጀመሪያ ዲግሪ (BA) በኢኮኖሚክስ፣ ማርኬቲንግ፣ ማኔጅመንት፣ ቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ወይም በተዛማጅ መስኮች።
• የሥራ ልምድ፡ በአስተዳደር፣ በማርኬቲንግ በሽያጭ አስተዳደር እና በአመራር እና በድርጅት ዕቅድ ዝግጅት ቢያንስ 3 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሥራ ልምድ ያለው/ላት።
ደመወዝ፡ 16,000ብር እና ለድርጅቱ ከሚያመጡት የሽያጭ ትርፍ ተከፋይ ይሆናል፡፡

ለማመልከት
ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች፣ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች ያለውን የጉግል ፎርም (Google Form) ሊንክ በመጠቀም ማመልከት ትችላላችሁ።
.ደሞዝ :16,000 ብር
• ቴሌግራም፦ @Supervacancy1
• ፎርም ለመሙላት፦ እዚህ ይጫኑ
• ስልክ፦ 0908 222223
• አድራሻ፦ ከመካኒሳ ወደ ጀርመን በሚወስደው መንገድ ላይ፣ የኪራይ ቤቶች ህንፃ፣ 2ኛ ፎቅ።