Welcome to our LMS Online Training Platform! At Bleqet, we believe that learning should be a lifelong journey, empowering individuals to expand their horizons and unlock their full potential. With our diverse range of courses, we offer a unique learning experience that caters to a wide array of interests and aspirations. Our dedicated team of trainers is committed to helping you acquire valuable skills and enhance your knowledge in various fields. Whether you're seeking personal development, looking to boost your sales techniques, dive into the world of digital marketing, explore the intricacies of programming or web development, master the art of photography, video editing, sound design, cinematography, or even delve into the world of interior design – we have the perfect course for you. Not only do our courses provide you with the opportunity to acquire new skills, but they also offer a pathway to generate additional income. We firmly believe that investing in yourself and continuously adding to your knowledge base can open doors to new career opportunities and financial growth. Our comprehensive curriculum includes in-demand topics such as Forex Trading, Stock Trading, Cryptocurrency, Business Strategies, Personnel Development, Basic Computer Skills, Advanced Skillsets, Language Learning, and much more. With our user-friendly Learning Management System (LMS), you can access our courses at your convenience. Seamlessly navigate through engaging multimedia content, interactive quizzes, and practical exercises, designed to enhance your learning experience and ensure your success. Join our vibrant community of learners who are passionate about self-improvement and growth. Together, let's embark on a transformative journey where knowledge knows no bounds. Invest in yourself. Learn with us today!
Bleqet – Empowering Minds, Inspiring Success.
እንኳን ወደ በልቀት የኦንላይን ሥልጠና ማዕከል በደህና መጡ!
በልቀት በተሰኘው የኦንላይን መማሪያ ማዕከላችን፣ መማር፣ ግለሰቦች አስተሳሰባዊ አድማሳቸውን እንዲያደረጁ እና ዕምቅ ችሎታቸውን በተግባር ማሳየት እንዲችሉ የሚያደርጋቸው በመሆኑ፣ የዕድሜ ልክ ጉዞ መሆን አለበት ብለን እናምናለን፡፡ የተለያዩ መስኮችን በሚዳስሱት ኮርሶቻችን አማካይነት፣ ዘርፈ ብዙ ፍላጎቶችን እና ጥያቄዎችን የሚመልስ በዓይነቱ የተለየ የመማር ዕድልን እናቀርባለን፡፡
ለሥራቸው በከፍተኛ ሁኔታ የሚተጉት አሰልጣኞቻችን፣ ተማሪዎች የጠቃሚ ክህሎቶች ባለቤት እንዲሆኑ እና በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን እውቀት ማስፋት እንዲችሉ አጥብቀው ይሠራሉ፡፡ ፍላጎትዎ፣ የግል ስብዕናዎን ማሳደግ፣ የሽያጭ ዘዴዎችዎን ማጎልበት፣ በቨዲጂታል ግብይት ዓለም ውስጥ ጠልቆ መግባት፣ ውስብስቡን የፕሮግራሚንግ ወይም የድረ ገጽ አሠራርን በጥልቀት ማወቅ፣ እንዲሁም በፎቶግራፍ ጥበብ፣ በቪዲዮ ኤዲቲንግ፣ በድምፅ ዲዛይን፣ በፊልም አሠራር (ሲኒማቶግራፊ)፣ ወይም ደግሞ በቤት ማሰዋብ (ኢንቲሪየር ዲዛይን) ዘርፍ ዘልቀው መግባት ሊሆን ቢችል እንኳን፣ ሁሉንም ፍላጎቶችዎን ሊያሟሉ የሚችሉ ኮርሶች አሉን፡፡
ኮርሶቻችን የአዳዲስ ክህሎቶች ባለቤት የሚሆኑበትን ዕድል ከማቅረባቸውም በላይ፣ ተጨማሪ ገቢ ሊያገኙ የሚችሉበትን መንገድም ያመቻቹልዎታል፡፡ በተለያየ ዘርፍ ያለዎትን አቅም ማሳደግና የእውቀት አድማስዎን ያለማቋረጥ ማስፋት፣ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን እና የገቢ ምንጮችን ይከፍታል የሚል ጠንካራ እምነት አለን፡፡
ሁሉን አቀፉ ሥርዓተ ትምህርታችን፣ የውጭ አገር ገንዘቦች ግብይትን (Forex Trading)፣ የስቶክ ግብይትን (Stock Trading)፣ ክሪፕቶ ከረንሲን (Cryptocurrency)፣ የንግድ ሥራ ስልቶችን (Business Strategies)፣ የሰው ሃብት ልማትን (Personnel Development)፣ መሰረታዊ የኮምፒውተር ክህሎቶችን፣ ከፍተኛ ክህሎቶችን፣ የቋንቋ ትምህርትን እና ሌሎች ወቅቱ የሚፈልጋቸውን መስኮች የሚያካትት ነው፡፡
ለተጠቃሚ ምቹ በሆነው የኦንላይን ትምህርት ሥርዓታችን (LMS) በመጠቀም የምንሰጣቸውን ኮርሶች ለእርስዎ በተመቸ ጊዜና ሁኔታ ማግኘት ይችላሉ፡፡ የመማር ልምድዎን ለማሻሻል እና ስኬትዎን ዕውን ለማድረግ በተዋቀሩ ቀልብን የሚገዙ የመልቲሚዲያ ይዘቶችን፣ አወያይ የሆኑ ጥያቄዎችን እና ተግባራዊ ልምምዶችን በጣም በቀላሉ ይጠቀሙባቸው፡፡
ራስን ለማሻሻል እና ለእድገት ከፍተኛ ፍቅር ያላቸውን ንቁ ተማሪዎቻችንን ይቀላቀሉ፡፡ ወሰን አልባ ወደሆነው የእውቀት ከፍታ የሚያደርስዎትን የለውጥ ጉዞ አብረውን ይጓዙ፡፡
ራስዎን ያሳድጉ፡፡ ዛሬውኑ ከእኛ ጋር መማር ይጀምሩ!