የሽያጭ ሱፐርቫይዘር

Application deadline closed.

Job Description

የስራ መደቡ፡ የሽያጭ ሱፐርቫይዘር

Super Boost-Up በዲጂታል ማርኬቲንግ እና በኦንላይን ትምህርት (LMS) ዘርፍ የሚሰራ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ነው።
ድርጅታችንን ወደ ስኬት ለመምራት የሚያስችል ከፍተኛ ልምድ እና ተነሳሽነት ያለውየሽያጭሰራተኛ ሱፐርቫይዘር እየፈለግን ነው። ተመራጩ እጩ በዲጂታል ማርኬቲንግ ላይ ጥልቅ ግንዛቤ ያለው እና ሽያጭ በማምጣት የተረጋገጠ የስራ ልምድ ያለው መሆን አለበት። እኛ ስልጠና የምንሰጠው ሳይሆን በቂ ልምድ ያለው እና ስራውን ተረድቶ በራሱ መስራት የሚችል፣ ለሽያጭ ግባችን አስተዋፅኦ ማድረግ የሚችል ኃላፊነት የሚሰማው ባለሙያ እንፈልጋለን። በተለይም የኦንላይን ትምህርት (LMS) መድረካችንን የኦንላይን የስራ ቅጥር በቅርቡ ለምናደርገው ምረቃ ስኬታማነት የበላይነትን መውሰድ የሚችል ሰው እንፈልጋለን።

ዋና ዋና ኃላፊነቶች፡-

· ሽያጭ እና ገቢ ማመንጨት፡ የኩባንያውን ሽያጭ በከፍተኛ ሁኔታ ለመጨመር እና የገቢ ግቦችን ለማሳካት ስልቶችን ማዘጋጀት እና መተግበር። ይህ ዋና ኃላፊነት ሲሆን፣ ሱፐርቫይዘሩ አዳዲስ ስራዎችን ማመጣት ዋናው ስራ ነው፡፡

· የኦንላይን ትምህርት (LMS) መድረክ ምረቃ እና አስተባባሪነት:

o የኦንላይን ትምህርት (LMS) መድረክ ምረቃ ዝግጅቶችን ሙሉ በሙሉ ማስተባበር እና ስኬታማነቱን ማረጋገጥ።

o ስፖንሰርሺፖችን መፈለግ እና ማምጣት።

o ዩ እንግዶችን መጋበዝ እና ምረቃው በትክክል እንዲካሄድ ማመቻቸት።

o ይህንን ፕሮጀክት ከዲጂታል ስራዎቻችን ጋር በማጣመር ስኬታማነቱን ማረጋገጥ።

· ስትራቴጂያዊ እቅድ እና አፈጻጸም፡ የድርጅቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማቀድ፣ ማደራጀት፣ አጠቃላይ የድርጅቱን ስራ ማቀድ፣ ማደራጀት፣ መምራት እና መቆጣጠር።

· የኤል.ኤም.ኤስ. ፕላትፎርም ይዘት ስራ መከታተል እና ጥራቱን ማረጋገጥ።

· ምልመላ እና አዲስ ሰራተኞችን ማቀናጀት (እንደ አስፈላጊነቱ)፡ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ አዳዲስ ሰራተኞችን በመመልመል፣ በማሰልጠን እና በመቅጠር ሂደት ውስጥ መሳተፍ።

መስፈርቶች፡-

· የመጀመሪያ ዲግሪ በኢኮኖሚክስ፣ ማርኬቲንግ፣ ማኔጅመንት፣ ቢዝነስ አስተዳደር፣ ወይም ተዛማጅ መስክ።

· በዲጂታል ማርኬቲንግ እና በሽያጭ ማምጣት የተረጋገጠ ሰፊ ልምድ ያለው።

· የኦንላይን ትምህርት (LMS) መድረኮችን የሚያውቅ እና የምረቃ ዝግጅቶችን የማስተባበር ችሎታ ያለው።

· ጥሩ የአመራር፣ የግንኙነት እና የሪፖርት አቀራረብ ክህሎት

ደመወዝ፡ 8,500 ብር እና 6% ኮሚሽን
• ቴሌግራም፦ @Supervacancy1
• ፎርም ለመሙላት፦ እዚህ ይጫኑ
. ስልክ፦ 0924908889
• አድራሻ፦ ከመካኒሳ ወደ ጀርመን በሚወስደው መንገድ ላይ፣ የኪራይ ቤቶች ህንፃ፣ 2ኛ ፎቅ።

Number Of Vacancies
3