የኮንቴንት ክሬተር እና ካስቲንግ ዳይሬክተር

March 15, 2026
10000 Br / month
Application deadline closed.

Job Description

የኮንቴንት ክሬተር እና ካስቲንግ ዳይሬክተር

ለማመልከት እባክዎ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ (Use this link to APPLY)

https://forms.gle/MfsRZvQNK59zDkmu5

ከከፍተኛ የፈጠራ ባለሙያዎች ጋር በመሆን ስምዎን የሚገነቡበት ትልቅ እድል!
ድርጅታችን በዲጂታል ማርኬቲንግ፣ በኦንላይን ስልጠና እና በማማከር ስራ ላይ የተሰማራ ቀዳሚ ተቋም ነው። አሁን ደግሞ ስራዎቻችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ፣ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በተሟላ የፕሮፌሽናል ፕሮዳክሽን ስቱዲዮ ውስጥ አብሮን የሚሰራ ብቁ ኮንቴንት ክሬተር እና ካስቲንግ ዳይሬክተር እንፈልጋለን።
በተለይም የተዋጣለት የፖድካስት (Podcast) ዝግጅት ልምድ ያላችሁ እና ራሳችሁን እንደ ብራንድ ማሳደግ የምትፈልጉ ባለሙያዎች ቅድሚያ እንሰጣለን።
እኛ የምናቀርባቸው ልዩ ጥቅሞች
• ዘመናዊ ስቱዲዮ፦ ሙሉ ጥራት ባላቸው የካሜራ፣ የድምፅ እና የብርሃን መሳሪያዎች የተደራጀ የቪዲዮ እና የፖድካስት ስቱዲዮ።
• የግል ብራንድ ግንባታ፦ ፕሮፌሽናል በሆነ መልኩ በቪዲዮዎች ላይ በመታየት ራስዎን ለገበያ የሚያስተዋውቁበት እድል።
• ምቹ የስራ አካባቢ፦ ስራን በስርአት እና በቴክኖሎጂ ለመስራት የሚያስችል የተደራጀ ቢሮ።
ዋና ዋና የስራ ኃላፊነቶች
• የፈጠራ ስራዎች፦ ለተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ገጾች (TikTok, Instagram, Facebook) የሚሆኑ አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ የቪዲዮ ሃሳቦችን ማመንጨት።
• ካስቲንግ እና ፖድካስት፦ ለቪዲዮ ቀረጻ የሚሆኑ ባለሙያዎችን መምረጥ (Casting) እና ልምድ ባለው መልኩ የፖድካስት/የቃለ-መጠይቅ ፕሮግራሞችን መምራት።
• የኮርስ ዝግጅት፦ ለኦንላይን ስልጠናዎች የሚሆኑ ማኑዋሎችን እና የትምህርት ይዘቶችን ማዘጋጀት።
• እቅድ ማውጣት፦ ሳምንታዊ እና ወርሃዊ የኮንቴንት ካላንደር ማዘጋጀት እና ስራዎችን መከታተል።
• ድምፅ እና ቪዲዮ፦ ፕሮፌሽናል የሆኑ የቮይስ ኦቨር (Voiceover) ስራዎችን መስራት እና በቪዲዮ ኤዲቲንግ ስራ ላይ መሳተፍ።
ተፈላጊ ችሎታዎች እና ዝግጅት
• ትምህርት፦ በመጀመሪያ ዲግሪ በJournalism, Communication, Marketing ወይም ተዛማጅ መስኮች የተመረቀ/ች።
• ልምድ፦ በዲጂታል ማርኬቲንግ እና በኮንቴንት ፈጠራ ቢያንስ የ2 ዓመት ልምድ ያለው/ላት።
• ተሰጥኦ፦ በካሜራ ፊት የመቅረብ ከፍተኛ በራስ መተማመን እና ተጫዋች ስብዕና (Sense of humor)።
• ቴክኒካዊ ችሎታ፦ በቪዲዮ ኤዲቲንግ (Premiere/CapCut) እና ግራፊክስ ዲዛይን (Photoshop/Canva) ላይ እውቀቱ ቢኖረው/ራት ይመረጣል።
እንዴት ማመልከት ይቻላል?
• ጾታ፦ ሴት
• ደመወዝ፦ 10,000 ብር (እንደ ችሎታው እና እንደ ስራው ጥራት የሚስተካከል)
ልምድዎን እና የሰሯቸውን ስራዎች (Portfolio) በሚከተሉት አድራሻዎች ይላኩ፦
• ቴሌግራም፦ @Supervacancy1
• ፎርም ለመሙላት፦ እዚህ ይጫኑ
• አድራሻ፦ ከመካኒሳ ወደ ጀርመን በሚወስደው መንገድ ላይ፣ የኪራይ ቤቶች ህንፃ፣ 2ኛ ፎቅ።
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ ትችላላችሁ።